Abstract:
በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት መማር ማስተማር ወቅት ስዕላዊ የትምህርት መርጃ መሳርያዎች መጠቀም ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡የዚህ ጥናት ኣላማ ከፊል ሙከራዊ የምርምር ዘዴን በመጠቀም የገብረ ጉራቻ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የገላጭ ድርሰት አጻጻፍ ኪሂል ላይ ያለውን ፋይዳ መፈተሸ ነው፡፡የጥናቱም አይነት ከፊል ሙከራዊ የምርምር ዘዴን በመጠቀም ሲሆን የጥናቱም ተሳታፊዎችም የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡አጥኚው ይህንን የሙከራ ዘዴን ያካሄደው በኦሮሚያ ክልል ገብረ ጉራቻ ከተማ ውስጥ የሚገኛው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመምረጥ ተችሏል፡፡ለጥናቱ ለመረጃ መሰብሰቢያነት አጥኚው የተጠቀመበት መሳሪያ የተማሪዎችን የገላጭ ድርሰት ፈተናን ነው፡፡ስልሳ (60) የታለሚው ትምህርት ቤት የናሙና ተመራጮችን ሁለት ጊዜ የድርሰት ምንነትና የአጻጻፍ ኪሂል ላይ መሰረት ያደረጉ ትምህርቶችን ከመሰናዶ ትምህርት ቤት በተመረጠው የአማርኛ ቋንቋ መምህር ትምህርቱ ተሰጥቷል፡፡እንዲሁም የታላሚው ትምህርት ቤት የናሙና ተመራጭ ተማሪዎች ፈተናው ከተሰጠ ቧኃላ በፈተናው ውጤት መሰረት ለናሙና የተመረጡት ተማሪዎች ባመጡት ውጤት መሰረት ተመሳሳይ ነጥብ ያመጡትን ተማሪዎች በሁለት ቡድን (በቁጥጥር ቡድን እና በሙከራ ቡድን) በመክፈል በተለያየ የመማር ማስተማር ዘዴ በመጠቀም ትምህርቱን በመስጠት እንዲሁም ለቡድኖቹ ተመሳሳይ ፈተና ለሁለተኛ ግዜ ተሰጥቷል፡፡የተማሪዎችም የፈተና ውጤት መሰረት በማድረግ የተገኘው የጥናቱ ውጤትም እደሚያመለክተው በስዕላዊ መርጃ መሳሪያ ሳይታገዙ የገላጭ ድርሰትን ትምህርትን የተማሩ የቁጥጥር ቡድን ተማሪዎች በስዕላዊ መርጃ መሳሪያ የገላጭ ድርሰት ትምህርትን የተማሩ የሙከራ ቡድን ተማሪዎች በቃላት አጠቃቀማቸው፣በአረፍተ ነገር አወቃቀሮች፣በአንቀጽ አደረጃጀቶች፣በስርዓተ ነጥብ አጠቃቀማቸው እና በምስል ከሳችነት ባህሪያቸው በተቀመጠላቸው አምስት መመዘኛ መስፈርት የተሻለ ውጤት ማምጣታቸውን የጥናቱ ውጤት ያረጋግጣል፡፡በዚህ ጥናትና ምርምር ውስጥ የጥናቱ ውስንነቶችና የመፍትሔ አቅጣጫዎችም ተብራርቷል፡፡በመጨረሻም ወደፊት የገላጭ ድርሰት የኣጻጻፍ ክሂልን ትምህርትን ውጤታማነት ሊያረጋግጡ የሚችሉ አስተያየቶችም ተብራርተዋል፡፡