dc.contributor.author | አዘነ ፣, ደምሴ | |
dc.date.accessioned | 2021-06-30T06:48:02Z | |
dc.date.available | 2021-06-30T06:48:02Z | |
dc.date.issued | 2013-02 | |
dc.identifier.uri | http://etd.dbu.edu.et:80/handle/123456789/611 | |
dc.description.abstract | የዚህ ጥናት ዋና አላማ በተመረጡ ሶስት የመንግስት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የሰባተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የመናገር ክሂል መልመጃዎች የክፍል ውስጥ አተገባበር ተገቢነት መፈተሽ ነው፡፡ የጥናቱ መነሻ ጥያቄዎችም .የሰባተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ ማስተማሪያ መፅሀፍት ውስጥ ለመናገር ክሂል መልመጃዎች የተሰጠው ትኩርት ምን ይመስላል?፣መምህራን የመናገር ክሂል መልመጃዎች የክፍል ውስጥ አተገባበር ጠንካራና ደካማ ጎኖች ምን ምን ናቸው? የመናገር ክሂል በመማሪያ ክፍል ዉስጥ ሲተገበር የመምህሩና የተማሪው ሚና ምን ምን ነበሩ? የሚሉት ናቸው፡፡ እነዚህን ጥያቄዎች በአግባቡ መመለስ እንዲቻልም አይነታዊ ምርምር ዘዴና ገላጭ ምርምር ንድፍ ተግባራዊ ተደርገዋል፡፡በሞረትና ጅሩ ወረዳ ከሚገኙት የመንግስት ትምህርት ቤቶች መካከል የወይራምባ፣የቦሎና የዋቢ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በአመቺ ናሙና፣አራት የአማርኛ ቋንቋ መምህራን በጠቅላይ ንሞና በዚሁ ክፍል የሚማሩ አንድ መቶ ሀምሳ ተማሪዎች በቀላል የእጣ ንሞና በድምሩ አንድ መቶ ሀምሳ አራት ተሳታፊዎች ተመርጠው የጥናቱ ተተኳሪ ሁነዋል፡፡ ለጥናቱ የሚያስፈልጉ መረጃዎችም መምህራኑ በክፍል ውስት ሲያስተምሩ ለአስራ ሁለት ክፍለ ጊዚያት የመከታተያ ቅፅ በመጠቀም ምልከታ በማድረግ፣ ለተማሪዎች አስራ አምስት ጥያቄዎችን የፅሑፍ መጠይቅ እንዲሞሉ በማድረግ፣ ለመምህራን ዘጠኝ ጥያቄዎችን ቃለ መጠይቅ በማድረግና በሰነድ ፍተሻ ተሰብስበዋል፡፡ መረጃዎቹ ከተሰበሰቡ በኋላ በሚያነሷቸው ጭብጦች ተከፋፍለውና ተደራጅተው ተተንትነዋል፡፡የጥናቱ ውጤትም መምህራን የመናገር ክሂልን በተግባር ከማስተማር ይልቅ በገለፃና በማብራሪያ ላይ ተመስርተው ማስተማር፣ መምህራን የትምህርቱን አላማ በግልፅ ለተማሪዎች አለማስተዋወቅ፣ ትምህርቱን ከመጀመራቸው በፊት የሚያዝናኑ ነገሮችን አለመጠቀማቸው፣ ለሁሉም ተማሪዎች እኩል የተሳተፎ እድል አለመስጠት፣ መምህራን የመናገር ክሂል መልመጃዎች አተገባበርን በተመለከተ የስራ ላይ ስልጠና ባለማግኘታቸው ተማሪዎች መናገርን በተግባር እንዲማሩ የማድረግ ሚናቸውን በአግባቡ እየተወጡ አለመሆኑን መገንዘብ ተችሏል፤ በተጨማሪም በማስተማሪያ መፅሐፉ ውስጥ ለማስተማሪያነት የቀረቡት የመናገር ክሂል ማስተማሪያ ስልቶች ጥቂት መሆናቸውና ከነዚህም መካከል መምህራን አዘውተረው የሚጠቀሙት የተወሰኑትን ብቻ ማለትም ክርክርን፣ የቡድን ውይይትና አንድ አንድ ጊዜ ጭውውትን እንደሆነና ለአንድ ክፍለ ጊዜ የተመደበው ሰዓት በቂ አለመሆኑን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡በአጠቃላይ የመናገር ክሂል ትምህርት መልመጃዎች መተግበር ባለባቸው አግባብ እየተተገበሩ አለመሆኑን የጥናቱ ውጤት ያስረዳል፡፡ በጥናቱም ከላይ ለተጠቀሱት ችግሮች ከላይ እስከ ታች የሚመለከታቸው የትምህርት ባለ ድርሻ አካላት ሁሉ ምን ምን ማድረግ እንዳለባቸው በመጨረሻ የመፍተሄ ሃሳቦችን ጠቁሟል፡፡ | en_US |
dc.language.iso | en | en_US |
dc.title | የ7ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የመናገር ክሂል መልመጃዎች የክፍል ውስጥ አተገባበር ፍተሻ፣በአማራ ክልል፣ በሰሜን ሽዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ በተመረጡ ሦስት የመንግስት ትምህርት ቤቶች ማሳያነት | en_US |
dc.type | Thesis | en_US |