Research Finding
http://etd.dbu.edu.et:80/handle/123456789/965
2024-03-28T19:34:43Z
-
የሴቶች ተሳትፎና ሚና በባህላዊ የግጭት መፍቻ ዘዴዎችና ተቋማት (በሰሜን ሸዋ ዞን በተመረጡ ወረዳዎች) (roles of women in conflict resolution)
http://etd.dbu.edu.et:80/handle/123456789/1021
የሴቶች ተሳትፎና ሚና በባህላዊ የግጭት መፍቻ ዘዴዎችና ተቋማት (በሰሜን ሸዋ ዞን በተመረጡ ወረዳዎች) (roles of women in conflict resolution)
ዮሴፍ (Yosef ), ጌትነት (Getnet),; ሠርካለም( Serkalem, ይገረሙ ( Yigeremu); ከበደ( kebede), ይመር ( Yimer); ዘቢባ (Zebiba), መንግስቴ Mengiste)
የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በሰሜን ሸዋ ዞን በተመረጡ ወረዳዎች በባህላዊ የግጭት መፍቻ ተቋማትና
ዘዴዎች ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎና ሚና መመርመር ነው፡፡ ጥናቱ ዓይነታዊ (qualitative) ሲሆን
ከመስክ የተገኙ መረጃዎችን ለመተርጎምና ለመተንተን በዋናነት እንስታዊነት (Feminism)፣ ሥነ ተረክ
(Narratology) የተባሉ ንድፈ ሀሳቦችን በመጠቀም የጽሑፍ ትንተና (Text analysis) ተደርጓል፡፡
የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎችም ምልከታ፣ቃለ መጠይቅ፣የጽሑፍ መጠይቅና ቡድን ተኮር ውይይት
ናቸው፡፡ የመረጃ ትንተናው እንዳመለከተው፣ በባህላዊ የግጭት መፍቻ ተቋማቱ ውስጥ የሴቶች ሚና
እጅግ ዝቅተኛ ነው፡፡ ድርድሩን፣ክርክሩን፣ውሳኔውንና እርቁን በዋናነት የሚመሩት ሽማግሌዎች ወንዶች
ናቸው፡፡ በጥናቱ እንደታየው ከባልና ሚስት ግጭቶች አንዱና ዋነኛው ስንፈተ ወሲብ ነው፡፡ ይህን የባልና
ሚስት ችግር ግልጽ አድርጎ ለሽማግሌ ለማቅረብ ባህሉ ባለመፍቀዱ የተነሳ የግጭቱ መንስኤ ሳይታወቅ
ከነችግሩ በግልግል መልክ ለማስማማት ጥረት ይደረጋል፡፡ ሌላው በጥናቱ የታየው ስርአተ ጾታዊ አድልዎ
ሰፊ የባህል መሰረት ያለው መሆኑን ነው፡፡ ይህም ከተረቶች፣ከምሳሌያዊ ንግግሮችና ከቃል ግጥሞች
መረዳት ተችሏል፡፡ በነዚህ የስነ ቃል ዘርፎች ውስጥ ስርአተ ጾታና ስልጣን መስተጋብር ፈጥረው
ታይተዋል፡፡ አባዊው ስርአት ሴቶች እውቀት፣ልምድ እና ጥበብ እንደሌላቸው ፍርድና ፍትህ መስጠት
እንደማይችሉ ለማሳየት ስነ ቃሎች አስተዋጽኦ አድረገዋል፡፡ ሊብራል እንስታውያን የስርአተ ጾታና
የስልጣን ኢ-ፍትሀዊነት መስተካከል አለበት ብለው ያምናሉ፡፡ ይህ የሚሆነውም ሴቶች በእውቀት እና
በልምድ ከወንዶች እኩል ተሳትፎ እንዲኖራቸው ሲደረግ ነው፡፡ ይህ ጥናትም ያረጋገጠው ይህንኑ ነው፡፡
ሴቶች በራሳቸውም ሆነ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚከሰቱ ግጭቶችን ለመፍታት በጎጥ፣ በቀበሌ፣
በከተማ፣ በወረዳ፣ በክልልና በፌደራል ደረጃ በማደራጀት በሽምግልናው ተቋም ላይ እንዲሳተፉና
የወሳኝነት ሚና እንዲኖራቸው በማድረግ ሰብአዊና ፖለቲካዊ መብቶቻቸውን የማስከበር ሀላፊነትና
ግዴታም እንዳለበቸው ጥናቱ የመፍትሄ ሀሳብ አቅርቧል፡፡
2022-01-01T00:00:00Z
-
Agriculture recovery project for the war affected communities of North Shewa Zone, Amhara Region, Ethiopia
http://etd.dbu.edu.et:80/handle/123456789/1020
Agriculture recovery project for the war affected communities of North Shewa Zone, Amhara Region, Ethiopia
Mekete, Bekele,; Girma, Teklehana; Tafesse, Altaye; Kassahun, Bekele
Farmers in the North Shewa zone of Amhara Regional State heavily depends on mixed
agriculture for their livelihoods. The war has caused tremendous damages and losses to the
productive assets and supportive agricultural infrastructures and makes the community
vulnerable to food insecurity. It has aggravated the socio-economic conditions of the population.
To curve the situation and improve the livelihood of affected communities a recovery projects
have been designed. The project is expected to contribute for the recovery and improvement of
food and nutrition security through the restoration of productive assets, agricultural
infrastructures and capacity building of affected communities and their institutions. The project
will focus on the nine war affected districts and communities of North Shewa zone. The potential
target groups will comprise about 10,000 households which directly or indirectly affected by the
conflict. The project comprised different components: recovery and improvement of crop and
livestock production by promoting relevant packages that include inputs and technical capacity
building, restoration of assets and infrastructures with their facilities. Support will be provided to
fill in some of the identified gaps and strengthen the beneficiary households and institutions. The
project is expected to be funded by the government, non-government organizations. In addition
the beneficiaries are also expected to contribute in cash or kind (such as labour contribution). An
estimated amount of about 4,186,537,224 Ethiopian Birr is required for the three years life time
of the project.
2022-01-01T00:00:00Z
-
በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን በትግራይ አሸባሪ ሀይል ወረራ ወቅት የማህበረሰብ ስነ-ልቦና የዳሰሳ ጥናት (2013-2014 ዓ.ም.) (Community Psychology)
http://etd.dbu.edu.et:80/handle/123456789/1019
በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን በትግራይ አሸባሪ ሀይል ወረራ ወቅት የማህበረሰብ ስነ-ልቦና የዳሰሳ ጥናት (2013-2014 ዓ.ም.) (Community Psychology)
ታረቀኝ (Tarekegn ), ደሳለኝ (Desalegn); ጌታሁን ( Getahun ), ሳህሌ (Sahile),; አያሌዉ (Ayalew ), ዘለቀ( Zeleke)
አጠቃሎ (Summary)
የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ማህበረሰብ የትግራይ ወራሪ ሃይል በከፈተዉ ጦርነት የስነ ልቦና ሁኔታዉ ምን እንደሚመስል መፈተሽ፤መተንተን እና ማሳየት ነዉ፡፡ ጥናቱን ለማከናወን የእጣ ናሙና
አመራረጥ ዘዴን (Lottery Method) በመጠቀም (ሴ=278፤ወ=599) በድምሩ የ877 ተሳታፊዎች ለጽሁፍ
መጠይቅ፤ኢላማ ተኮር (Purposive Sampling) በመጠቀም ደግም ተሳታፊዎችን ለቃለ-መጠይቅ እና ለአትኩሮት
የቡድን ውይይት ተመርጠዋል። የጽሁፍ እና የቃል መጠይቅ እንዲሁም የአትኩሮት የቡድን ዉይይት አይነተኛ
የመረጃ መሰብሰቢያ መሳርያዎች ነበሩ፡፡ በጽሁፍ መጠይቅ የተሰበሰቡት መረጃዎች መቶኛ/ Percentage/፣አማካይ
/Mean/፣ የአንድ ናሙና ቲ-ቴስት(one sample T-test) እና ቅደም ተከተል /Ranking order/ በመጠቀም
ተተንትነዋል፡፡ በቃለ-መጠይቅ እና በአትኩሮት የቡድን ውይይት የተሰበሰቡ መረጃዎችን ደግሞ ጭብጥ በማዉጣት
ተተንትነዋል፡፡ በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ማህበረሰብ የጦርነትና መሰል ወረራዎችን ከመመከት አንጻር አሁን
የሚገኝበት የስነ-ልቦና ሁኔታ እንደ አባቶቹ ጠንካራ ነዉ ያሉት 45.8%፤እየተሸረሸረ ነዉ ያሉት 26.6%፤ደካማ የሚባል
ነዉ ያሉት ተሳታፊዎች ደግሞ 113.6% ነበሩ፡፡ በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ማህበረሰብ አሸባሪዉ የትግራይ ወራሪ
ሃይል አማራን የማጥፋትና ለህልዉናዉ ስጋት የመሆኑን ተጨባጭ እዉነታ ማህበረሰቡ በሚገባ ተረድቶታል ያሉት
64.9% የቀሩት 35.1% ደግሞ ማህበረሰቡ በሚፈለገዉ ደረጃ አልተረዳዉም ብለዋል፡፡ በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን
ማህበረሰብ የጀግና አባቶቹን አኩሪ ታሪክና ገድል በመፈጸም አካባቢዉን እና እራሱን ከአሸባሪዉ የትግራይ ወራሪ
ሃይል በሚገባ መከላከል ካልቻለባቸዉ ምክንያቶች መካከል የመንግስት ቁርጠኝነት ማነስ፤በየአካባቢዉ ባንዳዎች
መኖር፤የአመራር ቅንጅትና ክፍተት መኖር፤ ወዘተ ነበሩ፡፡ በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ማህበረሰብ በጀግንነት
ባህሪያቶች ላይ ከ1983 ዓም በፊት የነበረዉ ትውልድ እና ከ1983 ዓም ወዲህ ባለዉ ትዉልድ መካከል በሁሉም
የጀግንነት መስፈርቶች ከ1983 ዓም በፊት የነበረዉ የአማራና የሰሜን ሸዋ ማህበረሰብ የተሻለ (አማካኝ=52.9635)
ሲሆን ያሁኑ ትዉልድ የጀግንነት ሁኔታ (አማካይ=39.8597) ነበር፡፡ በመሆኑም ለወጣቱ ትዉልድ ታሪክን በአግባቡ
እንዲማር በማድረግ የአባቶቹን የስነ-ልቦና ዉቅር እና የአባቶቹን ታሪክና ጀግንነት በማስተማር ትዉልዱን መገንባት
ያስፈልጋል በተጨማሪም የስነ-ልቦና እና የስነ-አዕምሮ ባለሙያዎች ሰዎች ላይ የደረሱትን አደገኛ የስነ-ልቦና ጠባሳዎች
የአጭር፤የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ እቅድ አዉጥቶዉ በመስራት ማህበረሰቡን ከደረሰበት የስነልቦና ችግር
እንዲወጣ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
2022-01-01T00:00:00Z
-
ማህበራዊ ትስስር ሚዲያ እንደ ቀውስ ተግባቦት ስልት፡ አማራ ክልል በሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ተተኳሪነት (Social Media as crisis communication strategies in the case of Ethiopian Public Universities)
http://etd.dbu.edu.et:80/handle/123456789/1018
ማህበራዊ ትስስር ሚዲያ እንደ ቀውስ ተግባቦት ስልት፡ አማራ ክልል በሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ተተኳሪነት (Social Media as crisis communication strategies in the case of Ethiopian Public Universities)
አዝዛቸው(Azzachew ), ወንዴ( Wondie); ዳዊት (Dawit), ግርማ (Girma); ከፋለ (Kefale), ንብረት (Nibret)
የዚህ ጥናት አላማ አማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ማህበራዊ ትስስር ሚድያን እንደ ቀውስ
ተግባቦት ስልት አተገባበራቸው ምን እንደሚመስል መዳሰስ ነው፡፡በጥናቱ አይነታዊና መጠናዊ የምርምር አቀራረብ
ስልት ተግባራዊ ሲሆን መጠይቅ፣ ቃለመጠይቅ፣ድህረገጽ ዳሰሳና ምልከታ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች ሆነው
አገልግለዋል፡፡ ኢላማዊ የናሙና አመራረጥ ዘዴ ተጠኝ ዩኒቨርሲቲዎችንና ለቃለ-መጠይቅ የዩኒቨርሲቲዎችን
ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተሮች ለመምረጥ ተግባራዊ ሲሆን ይሁንታዊ የናሙና አመራረጥ ዘዴ ደግሞ መጠይቅ
ለሚሞሉ ተማሪዎች ተግባራዊ ሆኗል፡፡ ሁነታዊ የቀውስ ጊዜ ተግባቦት የጥናቱ ንድፈ ሀሳብ ሆኖ አገልግሏል፡፡ የጥናቱ
ግኝት እንደሚጠቁመው አንደኛ ዩኒቨርሲቲዎች በአካባቢያቸው የክስተት ምልክቶች ቢኖሩም እንኳን ማህበራዊ
ትስስር ሚዲያውን በመጠቀም ከቀውስ በፊት የመከላከል ስራ ያልተሰራ ሲሆን በቀው ጊዜ ደግሞ የቀውሱን ስፋትና
ጥልቀት ለመቀነስ ሳይሆን ክስተት እንዳልተፈጠረ የማስተባበያ መረጃዎችን ብቻ አስተላልፈዋል፡፡ ለዚህም
ተጠቃሚው ወደ ማህበራዊ ሚድያ መድረክ ወስዶ መወያያ አጀንዳ አድርጎ እንድወያይበት በር ይከፍታል፡፡ሁለተኛ
የማህበረሰቡንና የተማሪዎችን አመለካከት፣ አስተሳሰብና ግንዛቤ ለማሳደግ አወንታዊ ተጽእኖ ያላቸውን ወቅታዊና
አዳድስ እውቀቶችንና ቴክኖሎጅን ለማስተላለፍ ሳይሆን ለተቋሙ ገጽታ ግንባታ ታሰቦ ልማታዊ መረጃዎችን ብቻ
ይለጥፉበታል፡፡ ሶስተኛ ተማሪዎች ማህበራዊ ትስስር ሚድያዎችን በተለይም ፌስቡክን በመረጃ
ወቅታዊነዊነቱ፣ቅጽበታዊነቱና ብዝሃነቱ በልዩነት የሚጠቀሙት ሲሆን ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ በተቃራኒው በቀውስ
ጊዜ መደበኛ ሚድያዎችን በትኩረት ይጠቀሙባቸዋል፡፡ይህ ደግሞ ተማሪዎች ለተለያዩ አሉባልታዎች ተጋላጭ
እንደሆኑ ያሳያል፡፡አራተኛ የቴክኖሎጅና የኢኮኖሚ እጥረት፣የበይነ መረብ ተደራሽነት አለመኖር፣ የተጠቃሚዎች
አመለካከትና ስሜታዊነት፣ብሄርተኝነት፣ የተማሪዎች መሰረታዊ የሚድያ አጠቃቀም ክሂል አለመኖሩ፣
ግላዊነት፣ስምአልባነትና የዋይፋይ አገልግሎት ተደራሽ አለመሆን ዩኒቨርሲቲዎች ማህበራዊ ትስስር ሚድያን እንደ
ውጤታማ የቀውስ ጊዜ ተግባቦት ስልት አድርጎ ለመጠቀም ተጽእኖዎች መሆናቸውን የጥናቱ ግኝት ይጠቁማል፡፡
2022-01-01T00:00:00Z